Windows 8.1 ቋንቋ በይነገጽ ጥቅል (LIP)
Windows 8.1 ቋንቋ በይነገጽ ጥቅል (LIP) ለአብዛኛዎቹ በሰፊው ጥቅም ላይ የዋሉ የ Windows 8.1 ክፍሎች በከፊል የተተረጎመ የተጠቃሚ በይነገጽ ይሰጣል።
ጠቃሚ! ከታች ቋንቋ ሲመርጡ ሙሉ የገጹ ይዘት ወደመረጡት ቋንቋ ይለወጣል።
ስሪት፡
1.0
የታተመበት ቀን፡
12/11/2013
የዶሴ ስም፡
LIP_am-ET-32bit.mlc
LIP_am-ET-64bit.mlc
የዶሴ መጠን፡
2.7 MB
4.1 MB
Windows ቋንቋ በይነገጽ ጥቅል (LIP) በጣም በሰፊው ጥቅም ላይ የዋሉ የ Windows ክፍሎችን ከፊል ትርጉም ያቀርባል። LIP ከተጫነ በኋላ፣ በዓዋቂዎች ያለ ጽሑፍ፣ የንግግር ሳጥኖች፣ የእገዛ እና ድጋፍ አርዕስቶች በ LIP ቋንቋው ይታያሉ። ያለተተረጎመው ጽሑፍ በ Windows 8.1 መሰረታዊ ቋንቋ ይሆናል። ለምሳሌ፣ የ Windows 8.1 እስፓኒሽኛ ስሪት ከገዙ፣ እና የካታልኛ LIP ከጫኑ፣ አንዳንድ ጽሑፍች በእስፓኒሽኛ ይቀጥላሉ። በአንድ ነጠላ መሰረታዊ ቋንቋ ላይ ከአንድ በላይ LIP መጫን ይችላሉ። Windows LIP በሁሉም የ Windows 8.1 ስሪቶች ላይ መጫን ይቻላል።