Trace Id is missing
ወደ ዋናው ይዘት እለፍ
በመለያ ይግቡ

የMicrosoft Office የስክሪን መረጃ ቋንቋ

የሚታዩትን ጽሑፎች – ተምሳሌታዊ ቁልፎች፣ ማውጫዎች እና የመልእክት ሳጥኖች የመሳሰሉትን – በሌላ ቋንቋ ለማሳየት የስክሪን መረጃ ቋንቋውን ይጠቀሙ።

ጠቃሚ! ከታች ቋንቋ ሲመርጡ ሙሉ የገጹ ይዘት ወደመረጡት ቋንቋ ይለወጣል።

  • ስሪት፡

    1.0

    የታተመበት ቀን፡

    8/4/2013

    የዶሴ ስም፡

    screentiplanguage_am-et_32bit.exe

    screentiplanguage_am-et_64bit.exe

    የዶሴ መጠን፡

    1.4 MB

    1.4 MB

    የሚታዩትን ጽሑፎች – ተምሳሌታዊ ቁልፎች፣ ማውጫዎች እና የመልእክት ሳጥኖች የመሳሰሉትን – ትርጉም በሌላ ቋንቋ ለማሳየትና ሰዎች ሊረዱት በማይችሉት ቋንቋ የተጫኑ የMicrosoft Office አፕሊኬሽኖችን መጠቀም እንዲችሉ ለመርዳት የስክሪን መረጃ ቋንቋውን ይለውጡ።


    ከአጠቃቀም ጋር ተያይዘው የሚያጋጥሙ ሁኔታዎችን የሚጠቁሙ ምሳሌዎች እነሆ፦
    • በሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች የሚሰጥ የቋንቋ እገዛ
    • እገዛ ሰጪ መሐንዲሶች በማያውቁት ቋንቋ እገዛ መስጠት ይችላሉ
    • Officeን በሌላ ቋንቋ ለጊዜው ብቻ ወይም ለተወሰነ ጊዜ የሚጠቀሙ ተጠቃሚዎች (ተንቀሳቃሽ ተጠቃሚዎች)
    • በጋራ የሚጠቀሙበት ኮምፒውተር የቋንቋ አጠቃቀም
  • የሚደገፉ ስርዓተ ክንውኖች

    Windows 7, Windows 8 Release Preview

    • የሚሠራባቸው የMicrosoft Office አፕሊኬሽኖች፦
        Microsoft Office Word 2013, Microsoft Office Excel 2013, Microsoft Office Outlook 2013, Microsoft Office PowerPoint 2013, Microsoft Office OneNote 2013, Microsoft Office Visio 2013, Microsoft Office Publisher 2013
    • የሚፈለገው ሶፍትዌር፦
        የምሥራቅ እስያና ውስብስብ ሥርዓተ ሆሄ ያላቸውን ቋንቋዎች ለመጫን አጋዥ ፋይሎች ሊያስፈልጉ ይችላሉ። ኮንትሮል ፓነል ውስጥ የሚገኘውን ‘የአካባቢና የቋንቋ አማራጮች’ የሚለውን በመጠቀም ይህንን ማድረግ ይቻላል።
  • ይህንን ከድረ-ገጽ የሚገለበጥ ፕሮግራም ለመጫን፦
    1. ለማስጀመር በዚህ ገጽ ላይ የሚገኘውን ከድረ-ገጽ ገልብጥ የሚለውን ተምሳሌታዊ ቁልፍ ይጫኑ።
    2. ከሚከተሉት ውስጥ አንዱን ያድርጉ፦
      • የመጫኑን ተግባር ወዲያውኑ ለማስጀመር አስጀምር የሚለውን ይጫኑ።
      • ከድረ-ገጽ የሚገለበጠውን ኮምፒውተርዎ ላይ ይዘው በኋላ ለመጫን ያዝ የሚለውን ይምረጡ።
      • የመጫኑን ተግባር ለመሰረዝ ሰርዝ የሚለውን ይጫኑ።

    የስክሪን መረጃ ቋንቋውን ለማጥፋት ወይም ለመለወጥ፦
    1. Office ላይ ያለውን ‘ፋይል’ የሚል ተምሳሌታዊ ቁልፍ ይጫኑና ‘አማራጮች’ የሚለውን ይምረጡ፣ ‘ቋንቋ’ የሚለውን ከመረጡ በኋላ የስክሪን መረጃ ቋንቋውን 'ከማሳያው (ዲስፕሌይ) ቋንቋ ጋር አመሳስል' ብለው ያስተካክሉ።

    ይህንን ከድረ-ገጽ የተገለበጠ ፕሮግራም ለማስወገድ፦
    1. መነሻው ማውጫ ላይ ኮንትሮል ፓነል የሚለውን ይምረጡ።
    2. ፕሮግራም መጨመር/ማስወገድ የሚለውን ሁለት ጊዜ ይጫኑ።
    3. ከተጫኑት ፕሮግራሞች ዝርዝር መካከል Microsoft Office የስክሪን መረጃ ቋንቋ የሚለውን ከመረጡ በኋላ ይወገድ ወይም ይጨመር/ይወገድ የሚለውን ይጫኑ። የመልእክት ሳጥን ሲመጣ ፕሮግራሙን ለማስወገድ መመሪያዎቹን ይከተሉ።
    4. ፕሮግራሙን በእርግጥ ማስወገድ እንደሚፈልጉ ለማረጋገጥ አዎን ወይም ይሁን የሚለውን ይጫኑ።