የታተመው፡ ሃምሌ 30፣ 2023
ውጤታማ፡- መስከረም 30፣ 2023
እነኝ ቃላቶች ("Terms") በእነዚህ ውሎች መጨረሻ ላይ የተዘረዘሩትን የእነዚያን የማይክሮሶፍት ተጠቃሚ ምርቶች፣ ድር ጣቢያዎች እና አገልግሎቶች አጠቃቀም ይሸፍኑ በዚ (https://www.microsoft.com/servicesagreement#serviceslist) (the "Services")። በእነዚህ ውሎች ላይ የተደረጉ ለውጦችን እንዲያውቁ ከተደረገ በኋላ የMicrosoft መለያ በመፍጠር፣ አገልግሎቶቹን በመጠቀም ወይም በመጠቀምዎን በመቀጠል እነዚህን ውሎች ተቀብለዋል።
1. የእርሶ ግላዊነት። የእርሶ ግላዊነት ለኛ ጠቃሚ ነው። እባኮን ይሄን ያንብቡ የ Microsoft ግላዊነት ፅሁፍ (https://go.microsoft.com/fwlink/?LinkId=521839) ("የ ግላዊነት ፅሁፍ") ከመሣሪያዎት እና ከእርሶ የምንሰበስበው የዳታ አይነት ይገልጻል ("ዳታ")፣ ዳታዎን እንዴት እንደ ምንጠቀም እና ዳታዎን ለመጠቀም የምንከተለው የህግ ማዕቀፍ። በተጨማሪ የግላዊነት ፅሁፋ ሚገልፀው፣ እንዴት Microsoft ይዘቶን እንደ ሚጠቀም፣ ከሌሎች ጋር ያለውን የእርሶን ንግግር፣ በእርሶ አማካኝነት ወደ Microsoft በአገልግሎቶቹ በኩል የገቡ ፖስቶች እና ፋይሎች፣ ፎቶዎች፣ ዶኩመንቶች፣ ድምፅ፣ የዲጂታል ስራዎች፣ ቀጥታ ስርጭቶች እና እርሶ ያስገቡት፣ ያሰራጩት፣ የሰሩት፣ ያመነጩት፣ ወይንም በአግልግሎት በኩል ያጋሩት ወይንም ይዘቶችን ለማመንጨት ያስገቡት ግበዓቶች ("የእርሶ ይዘት")። ህደቱ በፈቃደኝነት ላይ ሚመሠረት እና በህግ እስከተፈቀደ ድረስ ሲሆን፣ በነዚ ደንቦች በመስማማት፣ የ Microsoft ስብስብ፣ እንደዚሁም በ ግላዊነት ፅሁፍ እንደተገለፀው ይዘቶን እና ዳታዎን እንዲጠቀም ይስማማሉ። በተወሰኑ ምክኒያቶች፣ በግላዊነት ፅሁፍ ላይ እንደ ተገለፀው የእርሶን ፈቃደኝነት ልንጠይቅ እንችላለን እንደዚሁም የተለየ ማሳሰብያ እናቀርባለን።
2. የእርስዎ ይዘት። አብዛኞቹ አገልግሎታችን የእርሶን ይዘት እንዲሰሩ፣ ወይም እንዲያጋሩ ወይንም መሣሪያ ከሌሎች እንዲወስዱ ይፈቅድሎታል። የእርስዎ ይዘቶችን ባለቤትነት አንጠይቅም። የእርሶ ይዘት የእርሶ ሆኖ ይቆያል እናም ለእርሱም ተጠያቂ እርሶ ኖት።
3. የስነምግባር ደንብ። አገልግሎቶቹን ሲጠቀሙ ለስነ-ምግባሮ እና ስለ ይዘቶ ጠጠያቂ እርሶ ኖት።
4. አገልግሎቶቹን መጠቀም እና ድጋፍ።
5. የሶስተኛ-ወገን መተግበሪያዎችን እና አገልግሎቶን መጠቀም። አገልግሎቶቹ እራሳቸውን የቻሉ ሦስተኛ ወገኖችን (Microsoft ካልሆኑ ኩባንያዎችን ወይም ግለሰቦችን) ምርቶች፣ አገልግሎቶች፣ ድር ጣቢያዎች፣ አገናኞች፣ ይዘት፣ ቁሳቁስ፣ ጨዋታዎች፣ ክህሎቶች፣ የማቀናጃ መንገዶች፣ ቦትዎች ወይም መተግበሪያዎች ("የሦስተኛ ወገገን መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች") እንዲያገኙ ወይም በእጅዎ እንዲያስገቡ ሊፈቅዱልዎት ይችላሉ። በተጨማሪም በጣም በርካታዎቹ አገልግሎቶቻችን ከሦስተኛ ወገን መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች ጋር መስተጋብር እንዲፈጥሩ ወይም የእርስዎን ይዘት ወይም ውሂብ እንዲያጋሩ ያግዙዎታል፣ እናም የእኛን አገልግሎቶች ሲጠቀሙ የሦስተኛ ወገን መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች እንዲገኙ ትዕዛዝ እየሰጡ መሆኑን ይገነዘባሉ። ሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎቹ እና አገልግሎቶቹ ይዘትዎን ወይም ውሂብዎን አታሚው፣ አቅራቢው ወይም አከናዋኙ ዘንድ እንዲያስቀምጡ ሊያስችልዎ ይችላሉ። የሦስተኛ ወገን መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች ጭነው መጠቀም ከመቻልዎ በፊት የግላዊነት መመሪያቸውን እንዲቀበሉ ወይም የእራሳቸውን ውሎች እንዲቀበሉ ሊጠይቁዎት ይችላሉ። በMicrosoft በባለቤትነት የተያዙ ወይም በእራሱ የሚተዳደሩ የተወሰኑ Stores (ለምሳሌ Office Store፣ Microsoft Store በXbox ላይ እና Microsoft Store በWindows ላይ) የሚመለከቱ የመተግበሪያ ውሎችን በተመለከተ ክፍል 13.ለ. ላይ ይመልከቱ። ማንኛውንም የሦስተኛ ወገን መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች ለማግኘት፣ ለመጠቀም ወይም ለማገናኘት የMicrosoft መለያን ከመጠቀምዎ በፊት የሦስተኛውን ወገን ውሎች እና የግላዊነት መመሪያዎች መገምገም አለብዎት። ማናቸውም የሦስተኛ ወገን ውሎች ይህን ውል አይቀይሩትም። Microsoft እንደ የማንኛውም የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች ወይም አገልግሎቶች አካ የአእምሮአዊ ንብረት ጥበቃ ፈቃድ አይሰጥም። እነዚህን የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎችና አገልግሎቶች ሲጠቀሙ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋቶችንና ሃላፊነቶችን ሙሉ ለሙሉ ለመቀበል የተስማሙ ሲሆን Microsoft እርስዎ ሲጠቀሟቸው ለሚነሱ ማናቸውም ችግሮች ሃላፊነት የለበትም። በማንኛውም የሶስተኛ-ወገን መተግበሪያ ወይም አገልግሎቶች በኩል በሚመታ መረጃ Microsoft ኃላፊነት የለበትም ተጠያቂም አይደለም።
6. የአገልግሎት ተገኚነት።
7. አገልግሎቱ ወይም ሶፍትዌሩ ላይ የተደረጉ ማዘመኛዎችና በእነዚህ ደንቦች ላይ የተደረጉ ለወጦች።
8. የሶፍትዌር ፈቃድ። የተለየ የMicrosoft ፈቃድ ስምምነት ካልቀረበ በስተቀር፣ (ለምሳሌ ከWindows ጋር አብሮ የቀረበ የMicrosoft መተግበሪያ የሚጠቀሙ ከሆነ፣ የWindows ስርዓተ ክወናው የMicrosoft የሶፍትዌር ፈቃድ ውሎች ለዚያ ሶፍትዌርም ገዢ ይሆናሉ)፣ ማንኛውም የአገልግሎቶቹ አካል ሆኖ በእኛ የሚቀርብልዎት ሶፍትዌር በእነዚህ ውሎች መሰረት የሚተዳደር ይሆናል። በMicrosoft ወይም በአጋሮቹ በባለቤትነት ይተያዙ ወይም የሚተዳደሩ በተወሰኑ Stores አማካኝነት የሚገኙ መተግበሪያዎች (ለምሳሌ Office Store፣ Microsoft Store በWindows ላይ እና Microsoft Store በXbox ላይ የመሳሰሉት) ከታች ክፍል 13.ለ.i የቀረበው ይመለከታቸዋል።
9. የክፍያ ውሎች። አንድ አገልግሎት ከገዙ እነዚህ የክፍ ውሎች ግዢዎ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ ሲሆን በእነሱ ይስማማሉ።
10. ተቋራጭ አካል፣ የሕግ ምርጫ፣ እና የክርክሮች መፍቻ አካባቢ። ለነጻ እና ክፍያ ለሚጠይቁ የ Skype የምርት ስም ያላቸው አገልግሎቶች ፍጆታ አጠቃቀምዎ፣ እርስዎ ከአውሮፓ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከአፍሪካ ውጪ የሚኖሩ ከሆነ፣ ውል እየፈጸሙ ነው፣ እንዲሁም በእነዚህ ውሎች ውስጥ "Microsoft" የሚለው በሁሉም ላይ Skype Communications S.à.r.l, 23 – 29 Rives de Clausen, L-2165 Luxembourg ይወክላል ማለት ነው ከታች ካልተገለጸ በስተቀር። ለነጻ እና ክፍያ ለሚጠይቁ የSkype የምርት ስም ያላቸው አገልግሎቶች ፍጆታ፣ እርስዎ ከአውሮፓ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከአፍሪካ ውጪ የሚኖሩ ከሆነ፣ የለክሰምበርግ ሕግ የሕግ መርሆዎች መጣረስ ሳይወስነው የእነዚህን ውሎች አተረጓጎም ይገዛል እንዲሁም የውሎቹን ጥሰትም በሕግ ይጠይቃል። እርስዎ የሚኖሩበት አገር ወይም ክልል ህጎች ሌሎች የይገባኛል ጥያቄዎች ላይ በጠቅላላ ገዢ ህግ ይሆናል (የተጠቃሚዎች ጥበቃ፣ ተገቢ ያልሆነ ውድድርና ከውል ውጪ የሚነሱ ሃላፊነቶች ክሶች)። እርስዎ ከአውሮፓ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከአፍሪካ ውጪ የሚኖሩ ከሆነ፣ የSkype የምርት ስም ያላቸው አገልግሎቶች ፍጆታን በቀጥታ የሚመለከቱ ወይም ተዛማጅ የሆኑ ሁሉንም ክርክሮች በተመለከተ በለክሰምበርግ ፍርድ ቤቶች ልዩ ስልጣን እና መገኛ ላይ እርስዎ እና እኛ ሊሰረዝ በማይችል መልኩ ስምምነት እንፈጽማለን። ለሌሎች ሁሉም አገልግሎቶች፣ እርስዎ የሚዋዋሉት ተቋራጭ፣ ገዢው ሕግ፣ እና ክርክሮቹ የሚፈቱበት አካባቢ ቀጥሎ ይታያል፦
በአካባቢዎ ያለው ደንበኛዎ እነዚህ ደንቦች ቢኖሩም እንኳን የተወሰኑ የአካባቢው ህጎች ለመዳኘት ሊጠይቅ ወይም አለመግባባቱን በሌላ ቦታ እንዲፈቱ መብት ሊሰጥዎ ይችላል። ይህ በሚሆንበት ጊዜ የካባቢዎ የተጠቃሚዎች ህግ እስከሚፈቅደው ድረስ በክፍል 10 ውስጥ የተደነገጉት የህግና የቦታ ምርጫ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ።
11. ዋስትናዎች።
በተጨማሪም በሸቀጦቻችን ላይ ሊኖሩ ለሚችሉት ዋናዋና እንከኖች ገንዘብ ማስመለስ ወይም ማካካሻን መምረጥ ይችላሉ። ከዋና እንከን አነስ ያልሆነ የሸቀጥ ወይም የአገልግሎት እንከን ሲኖር፣ አግባብ በሆነ ጊዜ እንዲስተካከልልዎ የማድረግ መብት አለዎት። ይህ የማይደረግ ከሆነ የሸቀጦቹን ገንዘብ የማስመለስ እና የአገልግሎቱን ውል የማቋረጥ እንዲሁም ላልተጠቀሙበት ማንኛውም ድርሻ ገንዘብ የማስመለስ መብት አለዎት። በተጨማሪም በሸቀጦቹ ወይም አገልግሎቶቹ እንከን ምክንያት በእርግጥ ሊያጡ ለሚችሉትን ማንኛውንም ነገር ወይም ጉዳት ካሳ የማግኘት መብትም አለዎት።
12. የተጠያቂነት ገደብ።
13. ለአገልግሎት የተወሰኑ ደንቦች። ከክፍል 13 በፊትና በኋላ ያሉት ደንቦች በአጠቃላይ ለሁሉም አገልግሎቶች ተፈጻሚ ይሆናሉ። ይህ ክፍል ከአጠቃላይ ደንቦቹ ተጨማሪ የሆኑ ለአንድ አገልግሎት የተወሰኑ ደንቦችን ያካትታል። እነዚህ አገልግሎት-አቀፍ ውሎች ከአጠቃላይ ውሎቹ ጋር ግጭት በሚፈጠር ጊዜ ገዥዎች ይሆናሉ።
14. አጠቃላይ ድንጋጌዎች። ይህ ክፍል እና ክፍል 1፣ 9 (እነዚህ ውሎች ከማብቃታቸው በፊት ለሚኖር መጠን)፣ 10፣ 11፣ 12፣ 15፣ 17 እና እነዚህ ውሎች ካበቁ በኋላ በእራሳቸው ውል ተፈጻሚነት የሚኖራቸው ውሎች እነዚህ ውሎች ካበቁ ወይም ቀሪ ከሆኑ በኋላም የሚቀጥሉ ይሆናል። ተፈጻሚ በሆነው ህግ እስከሚፈቀደው መጠን ድረስ በሙሉም ሆነ በከፊል፣ በማንኛውም ጊዜ ለእርስዎ ማሳወቅ ሳይጠበቅብን እነዚህን ውሎች ለሌላ ሰው ልናስተላልፍ፣ በእነዚህ ውሎች ስር ያሉብንን ግዴታዎች ለሌላ ሰው በንዑስ ውል ልናስተላልፍ፣ ወይም በእነዚህ ውሎች ውስጥ ያሉንን መብቶች ለሌላ አካል ንዑስ ፈቃድ ልንሰጥባቸው እንችላለን። እነዚህን ውሎች አሳልፈው ሊሰጡ ወይም አገልግሎቶቹን ለመጠቀም ማናቸውንም አገልግሎቶች ሊያስተላልፉ አይችሉም። ይህ እርስዎ አገልግሎቱን እንዲጠቀሙ በእርስዎና በ Microsoft መካከል የተደረገው አጠቃላይ ውል ነው። ይህ ውል የአገልግሎቱን አጠቃቀምዎን በተመለከተ በእርስዎና በ Microsoft መካከል ከአሁን በፊት የተደረገ ማንኛውም ውል በመሻር ተፈጻሚ ይሆናል። ወደነዚህ ውሎች በሚገቡበት ወቅት በዚህ ውል ላይ በግልጽ ከተቀመጡት በስተቀር በሌላ በማንኛውም መግለጫ፣ ውክልና፣ ዋስትና፣ መረዳት፣ ቃል ኪዳን ወይም ማስተማመኛ ላይ ተማምነው አይደለም። ሁሉም የእነዚህ ደንቦች ክፍሎች በተገቢው ህግ በሚፈቀደው ከፍተኛው መጠን ተፈጻሚ ይሆናሉ። አንደ ፍርድ ቤት ወይም የግልግል ዳኛ የነእዚህን ውሎች አንድ ክፍል እንደተጻፈው መተግበር እንደማንችል ከወሰነ እነዚህን ድንጋጌዎች በተገቢው ህግ ስር መፈጸም እስከከሚችለው ድረስ በሌሎች ተመሳሳይ ድንጋጌዎች እንተካቸዋለን። ነገር ግን የውሉ ቀሪ ድንጋጌዎች አይለወጡም። እነዚህ ደንቦች ሙሉ በሙሉ ለእርስዎና ለእኛ ጥቅም ናቸው። እነዚህ ደንቦች ከ Microsoft ወራሾችና ተሹዋሚዎች በስተቀር ለማንም ሌላ ሰው ጥቅም አይደሉም። የክፍል ርእሶች ለማጣቀሻ ብቻ ሲሆኑ ምንም የህግ ውጤት የላቸውም።
15. የይገባኛል ጥቄዎች በአንድ አመት ውስጥ መሞላት አለባቸው። የአካባቢዎ ህግ የይገባኛል ጥያቄዎችን ፋይል ለማድረግ የረዘመ ጊዜ እንዲኖር የሚያስገድድ ካልሆነ በስተቀር፣ ከእነዚህ ውሎች ወይም አገልግሎቶች ጋር የሚያያዝ ማንኛውም የይገባኛል ጥያቄ ፋይል ለማድረግ ከሚችሉበት ጊዜ ጀምሮ በአንድ ዓመት ውስጥ ለፍርድ ቤት (ወይም ክፍል 10.መ ተፈጻሚ የሚሆን ከሆነ ለድርድር) ፋይል መደረግ አለበት። በዚያ ጊዜ ውስጥ ካልተሞላ በቋሚነት ይታገዳል።
16. ወደ ውጪ የመላክ ህጎች። ሁሉንም ሶፍትዌሩ እና/ወይም አገልግሎቶቹ ላይ ተፈጻሚ ሊሆኑ የሚችሉ በመዳረሻዎች፣ በመጨረሻ ተተቃሚዎችና በመጨረሻ አገልግሎቶች ላይ ገደብን የሚካትቱ የአገር ውስጥና አለም አቀፍ ወደ ውጪ የመላክ ህጎችና መመሪያዎች ማክበር አለብዎ። በጂኦግራፊያዊና በወደውጪ መላክ ገደቦች ላይ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት https://www.microsoft.com/exporting ይጎብኙ።
17. መብትን መጠበቅ እና ስለ ግብረመልስ። በእነዚህ ውሎች ስር በግልጽ ከተቀመጠው በስተቀር፣ በማንኛውም የአዕምሮ ንብረት ማስከበሪያ፣ ዕውቀት፣ የቅጅ መብት፣ የንግድ ምስጤሮች፣ የንግድ ምልክቶች ወይም ሌላ በMicrosoft ወይም በማንኛውም ተዛማጅ አካል የተያዙ ወይም ቁጥጥር ስር ያሉ የአ ዕምሯዊ ንብረቶች፣ ማንኛውንም ስም፣ የንግድ ምስል፣ አርማ ወይም እኩያዎችን ጨምሮ ነገርን ግን በዚያ ሳይወሰን በእነዝህ ሁሉ Microsoft ለእርስዎ የፈቃድም ሆነ ሌላ ማንኛውም መብት አይሰጥም። ለአዲስ ምርት የሚሆኑ ሃሳቦች፣ ቴክኖሎጂዎች፣ ማስተዋወቆች፣ የምርት ስሞች፣ የምርት ግብረመልስ እና የምርት ማሻሻል ጨምሮ ማንኛውንም ሃሳብ፣ ጥቆማ ወይም አስተያየት ወይም ግብረመል ("ግብረመልስ") ለMicrosoft ቢሰጡ፣ Microsoft ለእርስዎ ክፍያ፣ የሮያሊቲ ወይም ሌላ ለእርስዎ የሚገባው ግዴታ ሳይኖርበት በነጻ የእርስዎን ግብረመልስ በማንኛውም መንገድ እና ለማንኛውም ተግባር በመጠቀም ተያያዥ ስራዎችን እንዲሰራ፣ እንዲያጋራ እና ለንግድ ስራ እንዲያውል መብት ሰጥተዋል። Microsoft የእርስዎን ግብረመልስ በማካተቱ ሶፍትዌሮቹን፣ ቴክኖሎጂዎችን ወይም ሰነዶቹን ለሌላ ሶስተኛ አካል ፈቃድ እንዲሰጥ ለሚያስገድድ ፈቃድ ተገዥ የሆነ ግብረመልስ አይሰጡም።
የአእምሮአዊ ንብረት መብት ጥሰት ክሶችን ለማቅረብ ማሳወቂያዎችና ስነ ስርዓቶች። Microsoft የሶስተኛ ወገኖች የአአምሮአዊ ንብረት መብቶችን ያከብራል። የቅጂ መብት ጥሰትን የሚመለከት ክስን ጨምሮ የአእምሮአዊ ንብረት መብት ጥሰት ማሳወቂያን መላክ የሚፈልጉ ከሆነ እባክዎ የጥሰት ማሳወቂያዎችን ለማቅረብ የምንጠቀምባቸውን ስነ ስርዓቶች ይጠቀሙ። የጥሰት ማሳወቂያዎችን (https://www.microsoft.com/en-us/legal/intellectualproperty/infringement) የዚን ደንቦች አካል የትኛው ሂደቶች ነው የሚሰራው። ከእዚህ የአሰራር ሂደት ጋር ተዛማጅ የሆኑ መጠይቆች ብቻ ምላሽ ያገኛሉ።
Microsoft በ ርእስ 17፣ የዩናይትድ ስቴትስ ኮድ፣ ክፍል 512 እና ተግባራዊ ሚሆንበት ቦታ፣ ምዕራፍ III የ (EU) 2022/2065 ህግች ውስጥ የተጠቀሰውን የቅጂ መብት ጥሰቶችን የተመለከቱ ማሳወቂዎች ሲሰጡ ምላሽ የሚሰጥበትን ሂደት ይጠቀማል። አስፈላጊ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ Microsoft በተደጋጋሚ ጥሰቶችን የሚፍጽሙ የ Microsoft አገልግሎቶች ተጠቃሚዎች መለያዎችን ሊያሰናክል ወይም ሊያቋርጥ ይችላል። በተጨማሪም አስፈላጊ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ Microsoft በግለሰቦች የተላኩ በሂደት ላይ ያሉ ማሳወቂያዎች ወይንም በኣካላት የተላኩ ያልተገኙ ማሳወቂያዎች ሊያግድ ይችላል። ለተሰጠ አገልግሎት የመተግበሪያ ሂደት የበለጠ ማብራሪያ፣ የዚኛው ሂደት አካል ሆኖ በ Microsoft የተወሰደ ውሳኔ ካሳን ጨምሮ፣ ምናልባት እዚ ይገኛል የጥሰት ማሳወቂያዎች (https://www.microsoft.com/legal/intellectualproperty/infringement)።
በማስታወቂያ ውስጥ የአእምሮአዊ ንብረት ስጋቶችን የተመለከቱ ማሳወቂያዎችና ስነ ስርዓቶች። እባክዎ በማስታወቂያ አውታረ መረባችን ላይ ስላሉ የአእምሮአዊ ንብረት ስጋቶችን በተመለከተ የአእምሮአዊ ንብረት መመሪያዎችን (https://go.microsoft.com/fwlink/?LinkId=243207) ይመልከቱ።
የቅጂ መብትና የንግድ ምልክት ማስታወቂያዎች። አገልግሎቶቹ © Microsoft Corporation እና ወይም አቅራቢዎቹ One Microsoft Way, Redmond, WA 98052, U.S.A. የቅጂ መብት ጥበቃ የሚደረግላቸው ናቸው። ሁሉም መብቶች በህግ የተጠበቁ ናቸው። ውሎቹ ያካተቱት የMicrosoft የንግድ ምልክት እና የምርት ስያሜ መመሪያዎችን (https://www.microsoft.com/en-us/legal/intellectualproperty/trademarks/usage/general.aspx) (በየጊዜው በሚሻሻሉት መሰረት)። Microsoft እና ሁሉም የMicrosoft ምርቶች፣ ሶፍትዌር እና አገልግሎት ስሞች፣ አርማዎች እና ምልክቶች ዩናትድ ስቴትስ ውስጥ እና/ወይም በሌሎች ሀገሮች ያልተመዘገቡ ወይም የተመዘገቡ የMicrosoft ዕህት ኩባንያዎች ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ። ከዚህ በታች ሁሉንም የማያጠቃልል ቢሆንም የተመዘገቡ የMicrosoft የንግድ ምልክቶችን ያሳያል https://www.microsoft.com/en-us/legal/intellectualproperty/trademarks/EN-US.aspx። የእውነተኛ ኩባንኛዎች ስሞች እና ምርቶች የባለቤቶቻቸው የንግድ ምልክቶች ሊሆኑ ይችላል። ሁሉም በዚህ ደንቦች ላይ በግልጽ ያልተሰጡ መብቶች እንደተጠበቁ ናቸው። በተወሰነ የ Microsoft የድር ጣቢያ አገልጋይ ላይ ጥቅም ላይ የሚውል የተወሰነ ሶፍትዌር በከፊል የኢንዲፔንደንት JPEG ግሩፕ የስራ ውጤት ነው። Copyright © 1991-1996 Thomas G. Lane. ሁሉም መብቶች በህግ የተጠበቁ ናቸው። "gnuplot" ሶፍትዌር በተወሰኑ የMicrosoft ድር ጣቢያ አገልጋዮች ላይ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን የቅጂ መብቱ© 1986‑1993 Thomas Williams፣ Colin Kelley የተያዘ ነው። ሁሉም መብቶች በህግ የተጠበቁ ናቸው።
የህክምና ማስታወቂያ። Microsoft የህክምና ወይም ሌላ ምንም አይነት የጤና ጥበቃ ምክር፣ ምርመራ ወይም ህክምና አይሰጥም። ማንኛውንም አይነት የህክምና ችግር፣ አመጋገብ፣ የአካል ብቃት ወይም የደህንነት ፕሮግራም በተመለከተ ሁልጊዜም የሃኪምዎን ወይም ሌላ ብቃት ያለው የጤና እንክብካቤ ሰጪ ባለሞያን ምክር ያግኙ። በአገልግሎቶቹ ላይ ወይም በእነሱ ውስጥ ባገኙት መረጃ ምክንያት በፍጹም የባለሞያን የህክምና ምክር ችላ አይበሉ ወይም ምክር መጠየቅዎን አያዘግዩ።
የአክሲዮን ጥቅሶችና የማውጫ ውሂብ (የማውጫ ዋጋዎችን ጨምሮ)። የፋይናንስ መረጃ በአገልግሎቶች በኩል የሚቀርበው ለግል ለንግድ ላልሆነ ጥቅምት የሚውል ብቻ ነው። ምናልባት የትኛውንም የገንዘብ ሰነድ የወይንም የሶስተኛ ወገን ፈቃድ ከ መስፈፀም፤መፍጠር፤እስፖንሰርነት፤መነገድ፤መሸጥ ወይንም የትኛውንም የፋይናንስ መሣሪያዎችን ወይም የኢንቨስትመንት ምርቶችን ማስተዋወቅ (ለምሳሌ በዝርዝሮች፣ ቅጂዎች፣የተቀረፁ ምርቶች፣የእንቨስትመንት ድጎማዎች፣የመለዋወጥ ንግድ ድጎማዎች፣የእንቨስትመንት ፖርትፎልዮዎች እና ወዘተ. ሂሳቡ መመለሻው እና/ወይንም የእቃው አቅም ወይንም የእንቨስትመንት ምርቶች የተመሠረቱት፣የተዛመዱት፣ ወይንም የሚከታተሉት ማንኛውንም የፋይናንስ ሰነድ ነው) ጋር በተያያዘ ከሶስተኛው ወገን ባለፈቃድ ጋር የተለየ የፅሁፍ ስምምነት ካሎት በስተቀር መጠቀም አይችሉም።
ገንዘብ ነክ ማሳወቂያ። Microsoft በፌዴራል የሴኪዩሪቲስ ህግ ወይም በሌሎች አገሮች የሴኪዩሪቲስ ህጎች የተመዘገበ ደላላ ወይም የመዋእለ ነዋይ ፈሰት አማካሪ ስላልሆነ ሴኪዩሪቲዎችን ወይም ሌሎች ገንዘብ ነክ ምርቶችን ወይም አገልግሎቶች ላይ ኢንቨስት የማድረግን፣ የምግዛትን ወይም የመሸጥን ተመካሪነት በተመለከተ ለግለሰቦች ምክር መስጠት አይችልም። በአገልግሎቶቹ ውስጥ የተካተተ ማንኛውም ነገር ማናቸውንም ሴኪዩሪቲ የመግዛት ወይም የመሸጥ ጥያቄ ወይም ማግባባት አይደለም። Microsoft እና የአክሲዮን ጥቅስ ፈቃድ ሰጪዎቹ ወይም የማውጫ ውሂብ አቅራቢዎቹ ማንኛውምን አይነት የተወሰነ ገንዘብ ነክ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች አይደግፉም ወይም አይመክሩም። በአገልግሎቶቹ ውስጥ ካሉት ነገሮች አንዳቸውም እንደ የባለሙያ ምክር እንዲያገለግሉ የታሰቡ አይደሉም፣ በዚያ ሳይገደብ ፣ የኢንቨስትመንት እና የግብር ምክሮችን ጨምሮ፡፡
ስለ H.264/AVC፣ እና VC-1 የቪዲዮ ደረጃዎች የተሰጠ ማሳወቂያ ሶፍትዌሩ በMPEG LA, L.L.C ፈቃድ ሊሰጣቸው የሚችሉ H.264/AVC፣ እና/ወይም VC-1 ኮዴክ ቴክኖሎጂን ሊያካትት ይችላል። ይህ ቴክኖሎጂ የውሂብ ማጨቂያ ቪዲዮ መረጃ ቅርጸጽ ነው። MPEG LA, L.L.C. ይህንን ማሳወቂያ ይጠይቃል:
ይህ ምርት በ H.264/AVC፣ እና VC-1 የፓተንት ፖርትፎሊዮ ፈቃዶች ስር ለግልና ለንግድ ላልሆኑ አገልግሎቶች (ሀ) ቪዲዮን ከደረጃው ጋር በሚጣጣም መልኩ ኢንኮድ ለማድረግ ("የቪዲዮ ደረጃዎች") እና/ወይም (ለ) በግልና ንግድ ባልሆነ እንቅስቃሴ ውስጥ የተሰማራ ተጠቃሚ ኢንኮድ ያደረጋቸውን እና/ወይም እንደዚህ አይነት ቪዲዮዎችን የማቅረብ ፈቃድ ካለው ቪዲዮ አቅራቢ የተገኙ የ H.264/AVC፣ MPEG-4 VISUAL እና VC-1 ቪዲዮዎች ኮዲንግ መፍታት። ምንም ፈቃድ ለሌላ ለማንኛውም አገልግሎት አልተሰጠም እንደተሰጠም መቆጠር የለበትም። ተጨማሪ መረጃ ከ MPEG LA, L.L.C. ማግኘት ይቻላል። ይመልከቱት MPEG LA ገፅ (https://www.mpegla.com)።
ለማስረጂያ አላማዎች ብቻ ይህ ማሳወቂያ በእነዚህ ውሎች ስር የሚከተሉትን የማያካትቱ ለዚያ ንግድ የግል ለሆኑ ለመደበኛ የንግድ አገልግሎቶችን አይገድብም (i) ሶፍትዌሩን ለሶስተኛ ወገኖች ዳግም ማሰራጨት ወይም (ii) ለሶስተኛ ወገኖች ለማሰራጨት ደረጃቸውን የጠበቁ ቪዲዮዎችን በሚጠብቁ ቴክኖሎጂዎች ነገሮችን መፍጠር።
ስለ H.264/HEVC፣ የቪዲዮ ደረጃዎች የተሰጠ ማሳወቂያ። ሶፍትዌሩ የH.265/HEVC ኮድ ቴክኖሎጂን ሊያካትት ይችላል። Access Advance LLC ይህንን ማስታወቂያ ይፈልጋል፡-
ከተካተተበት፣ በዚህ ሶፍትዌር ውስጥ ያለው የH.265/HEVC ቴክኖሎጂ በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ የ HEVC የፈጠራ ባለቤትነት መብት የይገባኛል ጥያቄዎች ተሸፍኗል፡- PATENTLIST.ACCESSADVANCE.COM። ሶፍትዌሩን እንዴት እንዳገኛችሁት ላይ በመመስረት ይህ ምርት በ HEVC Advance Pattent ፖርትፎሊዮ ስር ፍቃድ ሊሰጥ ይችላል።
ይህ ሶፍትዌር በMicrosoft መሳሪያ ላይ ከተጫነ ተጨማሪ የፍቃድ መረጃ በሚከተለው አድራሻ ማግኘት ይቻላል፡- aka.ms/HEVCVirtualPatentMarking።
መደበኛ የመተግበሪያ ፈቃድ ውሎች
MICROSOFT STORE፣ MICROSOFT STORE በWINDOWS ላይ፣ እና MICROSOFT STORE በXBOX ላይ
እነዚህ የፈቃድ ደንቦች በእርስዎና በመተግበሪያ አዘጋጁ መካከል የሚደረጉ ስምምነቶች ናቸው። እባክዎ ያንብቧቸው። ማናቸውንም ዝማኔዎች እና የመተግበሪያ ደጋፊዎችን ጨምሮ፣ መተግበሪያው ከተለየ ውል ጋር የሚመጣና፣ ይህ ከሆነም እነዚያ ውሎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ካልሆነ በስተቀር፣ከMicrosoft Store፣ Windows Store፣ ወይም Xbox Store (እያንዳንዱም በፈቃድ ውሎች ውስጥ እንደ “Store” የተጠቀሰ) በሚያወርዷቸው መተግበሪያዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ።
መተግበሪያውን በማውረድዎ ወይም በመጠቀምዎ ወይም ከእነዚህ ውስጥ አንዱን ለማድረግ በመሞከርዎ እነዚህን ውሎች ይቀበላሉ። የማይቀበሏቸው ከሆነ ምንም መብት የሌለዎት ሲሆን መተግሪያውን ማውረድ ወይም መጠቀም የለብዎትም።
የመተግበሪያ አታሚ ማለት Store ውስጥ በተገለጸው መሰረት በመተግበሪያው ላይ ለእርስዎ ፈቃድ የሰጠው አካል ማለት ነው።
በእነዚህ የፈቃድ ውሎች ከተስማ ከዚህ በታች ያሉት መብቶች አሉዎት።
ይህ ገደብ ለሚከተሉት ተፈጻሚ ይሆናል:
በተጨማሪም የሚከተሉት ቢኖሩም ተፈጻሚ ይሆናል:
የሚከተሉት ምርቶች፣ መተግበሪያዎችና አገልግሎቶች በ Microsoft የአገልግሎቶች ስምነት የሚሸፈኑ ሲሆን በእርስዎ ገበያ ውስጥ ላይገኙ ይችላሉ።