Trace Id is missing

የአገልግሎቶችዎ ስምምነት ግልፅ ተደርጓል

የ Microsoft ኦንላይን ምርት ተጠቃሚዎችና አገልግሎቶች በተመለከተ የ Microsoft አገልግሎቶች ስምምነትን በማዘመን ላይ እንገኛለን። እነዚህን ዝማኔዎች እያደረግን ያለነው ውሎቻችንን ግልፅ ለማድረግና ለእርስዎ ግልፅ በሆነ መልኩ መቀጠሉን ለማረጋገጥ እንደዚሁም ደግሞ የ Microsoft ምርቶች፥ አገልግሎቶችና ገፅታዎችን ለመሸፈን ነው።

ከታች የተዘረዘሩት እነዚህ ዝማኔዎች፣ በ ሴፕቴምበር 30፣ 2023 ላይ ተፈጻሚ የሚደረጉ ይሆናሉ። ምርቶቻችንን ወይም አገልግሎቶቻችንን በሴፕቴምበር 30፣ 2023 ላይ ወይም በኋላ መጠቀምዎን ከቀጠሉ፣ በተዘመነው የ Microsoft አገልግሎቶች ስምምነት ተስማምተዋል ማለት ነው።

በተደጋጋሚ የተጠየቁ ጥያቄዎች

የ Microsoft አገልግሎቶች ስምምነት ምንድን ነው?

የ Microsoft አገልግሎቶች ስምምነት በእርስዎና በ Microsoft (ወይም ከተባባሪዎች አንዱ) የእርስዎን የኦንላይን Microsoft ተጠቃሚ ምርቶችና አገልግሎቶች የሚመራው ነው። የሚሸፍነው አገልግሎትና ምርቶችን ዝርዝር እዚህማየት ይችላሉ።

የ Microsoft አገልግሎቶች ስምምነት ሽፋን የማይሰጣቸው አገልግሎቶችና ምርቶች የትኞቹ ናቸው?

የ Microsoft አገልግሎቶች ስምምነት Microsoft 365 ለድርጅት፣ ለትምህርት ወይም ለመንግስት ደንበኞች፣ Azure፣ Yammer፣ ወይም Skype for Business ን ጨምሮ ለጅምላ ፍቃድ የሚሰጡ ደንበኞች የተሰጡ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን አይመለከትም። ደህንነት፣ ግላዊነት እና ተገዢነት በተመለከተ ለቁርጠኝቶች እንዲሁም በ Microsoft 365 ለቢዝነስ ላይ ተግባራዊ ለሚሆን ተዛማጅ መረጃ፣ እባክዎ የ Microsoft ማዕከልን በ https://www.microsoft.com/trust-center/product-overviewይጎብኙ።

የ Microsoft አገልግሎቶች ስምምነት ላይ Microsoft እያደረገው ያለው ለውጦች ምንድናቸው?

ዋናዋና የሆኑትን ለውጦች ማጠቃለያ እዚህአቅርበናል።

ሁሉንም ለውጦች ለማየት፣ ሙሉውን የ Microsoft አገልግሎቶች ስምምነት እንዲያነቡ እንመክርዎታለን።

እነዚህ ስምምነቶች ተፈፃሚ የሚሆኑት መቼ ነው?

የ Microsoft አገልግሎቶች ስምምነት ዝማኔዎች በሴፕቴምበር 30፣ 2023 ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ። እስከዚያው ጊዜ ድረስ ግን፣ የእርስዎ የአሁኑ ውሎች በነበሩበት ይቆያሉ።

እነዚህን ውሎች እንዴት እቀበላለሁ?

ሴፕቴምበር 30፣2023 ላይ ወይም በኋላ ምርቶቻችንን ወይም አገልግሎቶቻችንን ሲደርሱ በተዘመነው የ Microsoft አገልግሎቶች ስምምነት ተስማምተዋል። ካልተስማሙ ምርቶቹን እና አገልግሎቶቹን መጠቀም ማቋረጥ እና የ Microsoft መለያዎን ከሴፕቴምበር 30፣ 2023 በፊት መዝጋት ይችላሉ።